Telegram Group & Telegram Channel
+++ ሦስቱ ዛፎች +++

በአንድ ኮረብታ ጫፍ ላይ የተተከሉ ሦስት ዛፎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ዛፎች የወደፊት ተስፋቸውና ሕልማቸው ምን እንደሆነና ምን መሆን እንደሚፈልጉ መወያየት ጀመሩ፡፡

የመጀመሪያው ዛፍ ‹‹ታላቅ ንጉሥ የሚተኛበት አልጋ ለመሆን እመኛለሁ፡፡ ዙሪያዬን በልዩ ቅርጽ ተሠርቼ ሰው ሁሉ እንዲያከብረኝ ዝናዬ እንዲነገር እፈልጋለሁ›› አለ፡፡

ሁለተኛው ዛፍ ይኼን ሲሰማ የራሱን የተለየ ምኞት ተናገረ፡፡ ‹‹እኔ ደግሞ የምጓጓው ታላቅ መርከብ ሆኜ ለመሠራት ነው! በዓለም ላይ እጅግ ዝነኛ የሆኑ ነገሥታት በእኔ ላይ ተሣፍረው እንዲሔዱና ከጥንካሬዬ የተነሣ ሰዎች እኔ ላይ በመሳፈራቸው ያለ ሥጋት እንዲጓዙ ነው የምፈልገው!›› አለ - መርከብ ሆኖ በባሕር ላይ ሲንሳፈፍ በዓይነ ሕሊናው እየታየው፡፡

ሦስተኛው ዛፍ ግን ‹‹ዛፍነቴን ብተው ያንዘፍዝፈኝ›› አለ፡፡ ‹‹እኔ የምፈልገው ከዚሁ ሳልነቃነቅ ረዥም ዛፍ ሆኜ ወደ ላይ ማደግ ነው፡፡ እጅግ ከፍ ብዬ አድጌ የዛፎች ሁሉ ንጉሥ ሆኜ ፣ ለሰማይ እጅግ ቅርብ ሆኜ ሰዎች በእኔ መሰላልነት ወደ ገነት እንዲገቡና እኔን ባዩ ቁጥር ፈጣሪያቸውን እንዲያስታውሱ እፈልጋለሁ›› አለና ምኞቱን ተናገረ፡፡

ይህን ተነጋግረው እንደጨረሱ አናጢዎች ወደ እነዚህ ዛፎች መጡ

አንደኛው አናጢ የንጉሥ አልጋ ለመሆን የሚመኘውን ዛፍ ቀረብ አለና ካየው በኋላ ‹‹ይኼ ዛፍ ጠንካራ ይመስላል ፤ ወስጄ ለቤት ዕቃ ሠሪዎች እሸጠዋለሁ›› አለ፡፡ ይህን የሰማው ዛፍ ‹የንጉሥ አልጋ› ሆኖ የመሠራት ሕልሙ ዕውን እንደሚሆን በመተማመን ፈነደቀ፡፡ አናጢው ወስዶ የሸጠላቸው እንጨት ሠሪዎች ግን የዛፉን ሕልም ሳይረዱ የንጉሥ አልጋ አድርገው በመሥራት ፈንታ የከብቶች የሣር ድርቆሽ ማስቀመጫ ሣጥን አድርገው ሠሩትና በአንድ በረት ውስጥ ተጣለ፡፡

ሁለተኛው አናጢ የንጉሥ መርከብ እሆናለሁ ብሎ የሚመኘውን ዛፍ ቀረብ ብሎ አየውና ‹‹ይኼ ዛፍ ጠንካራ ይመስላል ፤ መርከብ ወደሚሠሩ ሰዎች ወስጄ ባሳየው ጥሩ ዋጋ ያወጣልኛል›› አለ፡፡ ዛፉ ‹ስዕለቴ ሠመረ› ብሎ ተደሰተ፡፡ ሆኖም መርከብ ሠሪዎቹ ምኞቱን ሳያውቁ ቆራርጠው ቆራርጠው በርከት ያሉ የዓሣ ማጥመጃ ጀልባዎችን ሠሩበት፡፡ መርከብ እሆናለሁ ብሎ የተመኘው ይህ ዛፍ ዓሣ አጥማጆችን ጭኖ እየተንሳፈፈ የንጉሥ መርከብ ሲያልፍ ተመልካች ሆነ፡፡

ሦስተኛውን ዛፍም በመጥረቢያ ሲቆርጡት የዛፎች ንጉሥ ሆኖ ከፍ ብሎ የማደግ ሕልሙን አብረው ቆረጡት፡፡

ከብዙ ዓመታት በኋላ አንዲት የጸነሰች ብላቴና ከአንድ አረጋዊ ጋር ቤተልሔም በሚባል የይሁዳ ከተማ መጣች፡፡ በወቅቱ የማደሪያ ሥፍራ ስላልነበር በከብቶች በረት ውስጥ ለማደር ገቡ ፤ ጸንሳ የነበረችውንም ልጇን በበረት ውስጥ ወለደችው፡፡ የመኝታ ሥፍራ ስላልነበር ሕጻኑን የከብቶቹ የሣር ድርቆሽ በሚቀመጥበት ሳጥን ውስጥ አስተኛችው፡፡ የዚያን ቀን ለተወለደው ሕጻን ከሩቅ የመጡ ነገሥታት ሳይቀር ሥጦታን አመጡለት፡፡ የንጉሥ አልጋ መሆን ይመኝ በነበረው ያ ዛፍ ሳጥን ሆኖ ቢሠራም የነገሥታት ንጉሥ መኝታ ሆነ፡፡

ይህ ከሆነ ከሠላሳ ዓመታት በኋላ የዓሣ ማጥመጃ ሆኖ በተሠራው ጀልባ ላይ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ዓሥራ ሦስት ሰዎች ተሳፈሩበት፡፡ የንጉሥ መርከብ ለመሆን የተመኘው ይህ ጀልባ በጀልባነቱ ዓሥራ ሦስት ተሳፋሪዎችን ተሸክሞ ሲማረር በጉዞ መካከል ድንገት ትልቅ ማዕበል ተነሥቶ መርከቧን ያናውጻት ጀመረ፡፡ ተሳፋሪዎቹ ጀልባዋን ለመቆጣጠር ታገሉ፡፡

ከመካከላቸው ግን አንዱ ተሳፋሪ ተኝቶ ነበር፡፡ ሞገዱ እየባሰ ሲመጣ የተኛውን ተሣፋሪ ‹‹ስንጠፋ አይገድህምን?›› ብለው ቀሰቀሱት፡፡ እሱም ተነሥቶ ማዕበሉን ገሠጸው፡፡ ጀልባው ድሮ እንደተመኘው የጫነው የነገሥታትን ንጉሥ እንደሆነ ተረዳ፡፡

ይህ ከሆነ ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ የዛፎች ንጉሥ ለመሆንና ወደ ሰማይ መውጫ መሰላል ለመሆን የተመኘውን ዛፍ አምጥተው ለአንድ ወንጀል ለሌለበት ንጹሕ አሸከሙት ፣ ከተራራ ጫፍ ሲደርሱም ባሸከሙት እንጨት ሰቀሉት፡፡ እንደተሰቀለ ምድር ለሦስት ሰዓታት ጨለመች ... ብዙ ተአምራት ተፈጸሙ፡፡ ይህ ዛፍ እንደተመኘው የዕጽዋት ሁሉ ንጉሥ ሆነ ፤ ሰዎች በእሱ መሰላልነት ወደ ገነት ገቡ ፤ እሱን ያዩ ሁሉ ፈጣሪያቸውን ያስታውሳሉ፡፡

በሁላችንም ሕሊና ውስጥ የእነዚህ ዛፎች ሕልም የተበላሸው ገና ያን ጊዜ ወዳላሰቡት ሥፍራ ሲጣሉ ነበር፡፡ ነገሩ አበቃ ብለን ስናስብ ግን የሦስቱም ምኞት ተሳካ፡፡ ይህ ጥንታዊ ታሪክ ምሳሌ እንጂ እውነተኛ ታሪክ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ ግን አንድ እውነታ አለ፡፡ በሕይወታችን ውስጥ እኛ አበቃልን ስንል እግዚአብሔር ሥራውን ይጀምራል፡፡

‹‹የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ያለቀ የተቈረጠ ነገርን በምድር ሁሉ መካከል ይፈጽማል።›› ኢሳ. 10፡23

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 2007 ዓ ም
ኩዌት የተጻፈ [ከሞት ባሻገር በተሰኘው መጽሐፍ የታተመ]

(ይህን በሥነ ጽሑፍ ዓለም የታወቀ ጥንታዊ ትረካ ያገኘሁት Archangel Michael Coptic Orthodox Church News letter (St. Mary Coptic Orthodox Church, East Brunswick, N.J./ volume 3 Feb. 2002) ዕትም ላይ ሲሆን ሃሳቡን ብቻ በመውሰድና አንዳንድ ለውጦች በማድረግ በዚህ መልኩ አስቀምጬዋለሁ፡፡ ይህ ታሪክ ምክር አዘል ምሳሌ ብቻ እንጂ ለተባሉት ዕቃዎችም ሆነ ለመስቀል ታሪካዊ አመጣጥ የሚጠቀስ ተአማኒ ታሪክ እንዳልሆነ አስታውሳለሁ፡፡)

tg-me.com/deaconhenokhaile/4303
Create:
Last Update:

BY የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280

Share with your friend now:
tg-me.com/deaconhenokhaile/4303

View MORE
Open in Telegram

የዲ ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

The Singapore stock market has alternated between positive and negative finishes through the last five trading days since the end of the two-day winning streak in which it had added more than a dozen points or 0.4 percent. The Straits Times Index now sits just above the 3,060-point plateau and it's likely to see a narrow trading range on Monday.

How Does Bitcoin Work?

Bitcoin is built on a distributed digital record called a blockchain. As the name implies, blockchain is a linked body of data, made up of units called blocks that contain information about each and every transaction, including date and time, total value, buyer and seller, and a unique identifying code for each exchange. Entries are strung together in chronological order, creating a digital chain of blocks. “Once a block is added to the blockchain, it becomes accessible to anyone who wishes to view it, acting as a public ledger of cryptocurrency transactions,” says Stacey Harris, consultant for Pelicoin, a network of cryptocurrency ATMs. Blockchain is decentralized, which means it’s not controlled by any one organization. “It’s like a Google Doc that anyone can work on,” says Buchi Okoro, CEO and co-founder of African cryptocurrency exchange Quidax. “Nobody owns it, but anyone who has a link can contribute to it. And as different people update it, your copy also gets updated.”

የዲ ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች from us

Telegram የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች
FROM USA